Article text
አመራር ወይም ትዕዛዝ የመስጠት መብት
፬፻፰
409 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ እናት ኩባንያ እንደባለአክሲዮን በጠቅላላ ጉባዔ
በሚሳተፍበት ጊዜ፣ በዲይሬክተሮች ቦርድ እንዱሁም
በከፍተኛ የሥራ አመራሩ አማካኝነት ለተቀጥላው
ኩባንያ አመራር ወይም ትዕዛዝ መስጠት ይችላል።
፪/ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፭፻፷፫ እና በዚህ አንቀጽ ንዐስ
አንቀጽ
(፫) ሥር የተመለከቱት ልዩ ሁኔታዎች
እንደተጠበቁ ሆኖ፤ የተቀጥላ ኩባንያው አመራር
በእናት ኩባንያው የተሰጠን ትዕዛዝ መፇጸም
አለበት።
፫/ በእናት ኩባንያው ምርጫ ሳይሆን በኩባንያው
መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በባለአክሲዮኖች ስምምነት
ወይም በማናቸውም ሕግ መሰረት የተሾሙ
ዲይሬክተሮች እና የሥራ አመራር አባላት እናት
ኩባንያው የሚሰጠውን ትዕዛዝ ለመከተል
አይገደደም።
፬/ ሙለ ለሙለ በእናት ኩባንያ ባለቤትነት ያልተያዘ
ተቀጥላ ኩባንያ ከእናት ኩባንያው በሚሰጥ ትዕዛዝ
መሰረት የሚመራ መሆን ወይም አለመሆኑን
በንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒቴር ወይም
፬፻፱
410 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በሚመለከተው ላላ አካል በሚያዘው የንግድ
መዝገብ ውስጥ በግልጽ ማሳወቅ አለበት።
፭/ ተቃራኒው እስካልተገለጸ ድረስ፣ ሙለ ለሙለ
በባለቤትነት የተያዘ ተቀጥላ ኩባንያ አመራር ከእናት
ኩባንያው መመሪያ ወይም ትዕዛዝ እንደሚቀበል
ግምት ይወሰዲል፤ ይህም ሲሆን ኩባንያው በንግድ
መዝገብ ውስጥ ማስገባት ያለበት ሙለ ለሙለ
በባለቤትነት ስለመያዙ ብቻ ይሆናል።