Article text
፩/ ከዕዲ ነጻ ለመደረግ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፯፻፺፱
የተቀመጡትን ሁኔታዎች የከሰረው ሰው ያሟላ
እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የከሰረው ሰው ከዕዲ
ነጻእንዱሆን ውሳኔ ይሰጣል።
፪/ ፍርድ ቤቱ ከዕዲ ነጻ ለመደረግ የቀረበውን አቤቱታ
ውድቅ ያደረገ እንደሆነ የከሰረው ሰው ከዕዲ ነጻ
ለመደረግ አቤቱታ ሉያቀርብ የሚችለው ፍርድ ቤቱ
ከዕዲ ነጻ መደረጉን ውድቅ ካደረገበት ቀን አንስቶ
ከአንድ ዓመት በኋላ ነው።
፫/ ባለዕዲው ከዕዲ ነጻ እንዱሆን ፍርድ ቤቱ የወሰነ
እንደሆነ ውሳኔው በንግድ መዝገብ ውስጥ
መመዝገብ አለበት። ከዕዲ ነጻ መደረግ በማንኛውም
መልኩ የባለዕዲውን ከንግድ መዝገብ መሰረዝን
አያስከትልም።
፬/ ባለዕዲው ከዕዲ ነጻ መደረጉን በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፉ
ስርጭት ባለው ጋዜጣ ላይ ማሳተም ይፇቀድለታል።
፮፻፶፬
655 ____________________________________________________ የንግድሕግ