Article text
፩/ የሥራ አስኪያጁን ሥልጣን የሚገድቡ
የዲይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔዎች ወይም ላልች
የውል ቃልች በንግድ መዝገብ ውስጥ እስካልገቡ
ድረስ ውጤት የሚኖራቸው በማህበሩ እና በሥራ
አስኪያጁ መካከል ብቻ ይሆናል።
፪፻፵
241 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) መሰረት ማህበሩ
በሥራ አስኪያጁ ሥራ የሚገደደው በቅን ልቦና
ከሥራ አስኪያጁ ጋር ውል የገቡ ሦስተኛ ወገኖችን
ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል ብቻ ነው።