Article text
፩/ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፺፩ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ላይ
የተደነገገው ቢኖርም አንድ ባለአክሲዮን በራሱ
ፇቃድ ካልሆነ በስተቀር በባለአክሲዮንነቱ ያገኛቸው
መብቶች ቀሪ አይሆኑም።
፪/ ከባለአክሲዮንነት የሚመነጩ መብቶች የሚባለት
በሕግ ወይም በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ መሰረት
በጠቅላላ ጉባዔው ወይም በዲይሬክተሮች ቦርድ
ውሳኔ ላይ ጥገኛ ያልሆኑ የማህበሩ አባል የመሆን፣
በስብሰባ የመካፇል፣ ድምፅ የመስጠት፣ የማህበሩን
ውሳኔ የመቃወም፣ ትርፍና ማህበሩ ሲፇርስ
፪፻፶፯
258 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በመጨረሻ በሚደረገው የሑሳብ ማጣራት ጊዜ
ከማህበሩ ሀብት ድርሻ የመካፇልና የመሳሰለት
መብቶች ናቸው።