Article text
፩/ በአንድ ውል ምክንያት የሚፇጠረው የጥቅም ግጭት
መጠን ከማህበሩ ሀብት አስር በመቶ እና ከዚያ
በላይ ሲሆን በቅድሚያ በጠቅላላ ጉባዔ
ስለሚፇቀድበት ሁኔታ በአንቀጽ ፫፻፺፬ ንዐስ አንቀጽ
(፬) እና ፫፻፺፭ ሥር የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ፤
በማህበሩ እና ከማህበሩ ጋር ቅርበት ባላቸው ሰዎች
ወይም ድርጅቶች መካከል የሚደረግ ስምምነት
በቅድሚያ በዲይሬክተሮች ቦርድ መፇቀድ አለበት፤
ቦርደ ስምምነቱን በሚያጸድቅበት ጊዜ የጥቅም
ግጭት ያለበት የቦርድ አባል ድምፅ መስጠት
አይችልም፤ የቦርደን ፇቃድ ሳያገኝ የሚደረግ
ስምምነት አይጸናም፤ ፇቃድ ከተሰጠም ጉዲዩን
ወዱያውኑ ኦዱተሮች እንዱያውቁት መደረግ
ይኖርበታል።
፪፻፯
208 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ ኦዱተሮች በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ
መሰረት በዲይሬክተሮች ቦርድ በተፇቀደት
ስምምነቶች ላይ ራሱን የቻለ ሪፖርት ለጠቅላላ
ጉባዔው ማቅረብ አለባቸው፤ በኦዱተሮች
የሚቀርበውም ሪፖርት ስለውለ ሁኔታ፣
የተፇፀመውን ክፍያ ዓይነትና መጠን፣እንዱሁም
ለጥቅም ግጭት ምክንያት የሆነውን የቅርበት
ሁኔታ የሚገልጽ በቂ መረጃ ማካተት ይኖርበታል፤
ጠቅላላ ጉባዔውም በሪፖርቱ መሰረት ተገቢ
የሆነውን ውሳኔ ሉሰጥ ይችላል።
፫/ ጠቅላላ ጉባዔው ያጸደቀውን ስምምነት ባለአክሲዮኖች
መቃወም የሚችለት በማህበሩ ላይ ከፍተኛ ጉዲት
የሚያደርስ ወይም ስምምነቱ በማታለል የተፇጸመ
ከሆነ ብቻ ነው።
፬/ ጠቅላላ ጉባዔው ስምምነቱን ያላጸደቀው በማህበሩ
ላይ ከፍተኛ ጉዲት የሚያደርስ ወይም ስምምነቱ
በማታለል የተፇጸመ በመሆኑ ምክንያት ካልሆነ
በስተቀር፤ የስምምነቱን ተፇጻሚነት አያስቀረውም፤
ስምምነቱ ማህበሩ ላይ ለሚያደርሰው ጉዲት
ማታለለን የፇጸመው ወገን እና ማታለለ
፪፻፰
209 ____________________________________________________ የንግድሕግ
መፇጸሙን ወይም ስምምነቱ በማህበሩ ላይ
ከፍተኛ ጉዲት የሚያደርስ መሆኑን እያወቁ ወይም
ማወቅ ሲገባቸው የፇቀደ የቦርድ አባላት
በአንድነትና በተናጠል ተጠያቂ ይሆናለ።
፭/ በዚህ አንቀጽ ከንዐስ አንቀጽ
(፩) እስከ
(፬) የተመለከቱት ድንጋጌዎች ማህበሩ ለማህበሩ ቅርበት
ካላቸው ሰዎች ጋር እንደማንኛውም ደንበኛ
በሚያደርጋቸው መደበኛ ስምምነቶች ላይ ተፇጻሚ
አይሆኑም።
፮/ ለዚህ አንቀጽ ዓላማ ለማህበሩ ቅርበት ያላቸው
ሰዎች ማለት የሚከተለትን ይጨምራል፡ሀ) የማህበሩ የቦርድ አባላት፤ ሥራ አስኪያጅ፣
ኦዱተር፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ አባላት፣ የማህበሩ
ፀሐፉዎች፤
ለ) በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፮)
(ሀ) ከተዘረዘሩት ሰዎች ጋር በፋደራል የቤተሰብ
ሕግ መሰረት የስጋና የጋብቻ ዝምድና
ያላቸው ሰዎች፤
ሐ) በዚህ አንቀጽ ንዐስ (፮)(ሀ) እና
(ለ) የተጠቀሱት ሰዎች አመራር፣ ባለድርሻ ወይም
፪፻፱
210 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ተጠቃሚ የሆኑበት የንግድ ማህበር ወይም
ድርጅት፤
መ) የማህበሩ እናት ወይም ተቀጥላ የሆነ ኩባንያ፤
ሰ) በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም በሕግ ያነሰ የድርሻ
መጠን ካልተቀመጠ በስተቀር፤ ከአስር በመቶ
ያላነሰ አክሲዮን ከማህበሩ የገዙ፣ማህበሩ
ባለአክሲዮን የሆነባቸው ወይም እርስ በእርሳቸው
አክሲዮን የተገዛዙ የንግድ ማህበራት፤
ረ) ላልች በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም በልላ ሕግ
ለማህበሩ ቅርበት አላቸው ተብለው የተጠቀሱ
ሰዎች።