Article text
፩/ ዕዲን መልሶ የማዋቀር ዕቅደ ዕዲን መልሶ በማዋቀር
ዘርፍ ባለሞያው ድጋፍ በባለዕዲው ይዘጋጃል፤
ገንዘብ ጠያቂዎቹ ዕዲን መልሶ የማዋቀር ዕቅደን
ለማሻሻል ጥያቄ የማቅረብ እና የአጸፊ-ሀሳብ
የማቅረብ መብት አላቸው።
፪/ ዕዲን መልሶ የማዋቀር ዕቅደ ዕዲን መልሶ በማዋቀር
ሥነ ሥርዓቱ ውስጥ በሚሳተፈ የሚመለከታቸው
ገንዘብ ጠያቂዎች በሙለ ተቀባይነት ማግኘት
አለበት፤
፫/ ዕዲን መልሶ የማዋቀር ዕቅደ የሚከተለትን ጉዲዮች
ሉያካትት ይችላል፡፬፻፹፮
487 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሀ) ለሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎች የክፍያ
ጥያቄዎች እንደገና የጊዜ ሰንጠረዥ
ማውጣት፤
ለ) የሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎችን
የክፍያ ጥያቄዎች መተው፤
ሐ) የገንዘብ ዕዲ ሰነድችን አወጣጥ በሚመለከቱ
ሕጎች መሰረት የገንዘብ ዕዲ ሰነድችን
በማውጣት የክፍያ ጥያቄዎችን መፍታት፤
መ) የሚመለከታቸውን ገንዘብ ጠያቂዎች የክፍያ
ጥያቄዎች ወደ አክሲዮን መቀየር፤
ሰ) የዚህ ሕግ አስገዲጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ሆነው በገንዘብ ጠያቂው ወይም በሦስተኛ
ወገን ኢንቨስተሮች የሚገዛውን የባለዕዲውን
ካፒታል መጠን መቀነስ ወይም
መጨመር፤
ረ) ለገንዘብ ጠያቂው ወይም ለሦስተኛ ወገን
ኢንቨስተሮች ነባር አክሲዮኖችን መሸጥ
ወይም አዱስ አክሲዮኖችን ማውጣት።