Article text
፩/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው መልሶ የማደራጀት
ዕቅደ በተቀላጠፇ መልኩ እንዱጸድቅ ለማመቻቸት
የሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎችን በተለያዩ
መደቦች ይከፊፍላል።
፪/ የገንዘብ ጠያቂዎች መደቦቹ በተጨባጭ መረጋገጥ
በሚችለ መስፇርቶች መሰረት የጥቅም
፭፻፵፩
542 ____________________________________________________ የንግድሕግ
መመሳሰልን የሚያንጸባርቁ መሆን አለባቸው፤
ቢያንስ ቢያንስ ዋስትና ያለው እና ዋስትና የላለው
የክፍያ ጥያቄ ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች በተለያዩ
መደቦች ውስጥ ተከፊፍለው መስተናገድ አለባቸው።
፫/ በባለዕዲው ንብረቶች ላይ የንብረት የዋስትና መብት
ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች በዋስትናነት የተያዘው
ንብረት ሲጣራ የሚኖረው ዋጋ ለማይሸፍነው
የክፍያ ጥያቄያቸው መጠን ዋስትና በልላቸው
ገንዘብ ጠያቂዎች መደብ ውስጥ ይሳተፊለ።
፬/ የግል ዋስትናዎች እና የመድን ዋስትናዎች ያሎቸው
ገንዘብ ጠያቂዎች ራሱን የቻለ መደብ ሉፇጥሩ
ይችላለ።
፭/ መልሶ የማደራጀት ዕቅደ በሰራተኞች የክፍያ
ጥያቄዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያደርግ ከሆነ የባለዕዲው
ሰራተኞች የራሳቸው የሆነ የተለየ መደብ
ይኖራቸዋል።
፮/ ባለአክሲዮኖች ገንዘብ ጠያቂዎች ባይሆኑም
የራሳቸው የሆነ የተለየ መደብ ይኖራቸዋል።
፭፻፵፪
543 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፯/ የመደቦቹ አከፊፇል እና ለመከፊፇል ጥቅም ላይ
የዋለት መስፇርቶች ለፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት
ሹም ገቢ ይደረጋል።
፰/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ውስጥ
የተመለከተው ቢኖርም ባለዕዲው አነስተኛ ወይም
መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆነ ባለዕዲው ወይም
መልሶ የማደራጀት ኃላፉው በሚያቀርቡት ጥያቄ
መሰረት ተቆጣጣሪ ዲኛው የሚመለከታቸው ገንዘብ
ጠያቂዎችን እና ባለአክሲዮኖችን በተለያዩ መደቦች
ከፊፍል ላለማስተናገድ ሉወስን ይችላል። ለዚህ
ድንጋጌ ዓላማ የግለሰብ ነጋዳ ወይም የንግድ
ማህበር እንደ አነስተኛ ወይም መካከለኛ
ኢንተርፕራይዝ ሆኖ የሚቆጠረው፡ሀ) ከአስር ያነሱ ሰራተኞች ካለት፤ ወይም
ለ) ባለፈት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ የነበረው
የሽያጭ ገቢ ከአምስት ሚሉዮን ብር በታች
ከሆነ (የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ እንደተጠበቀ
ሆኖ)፤ ወይም
፭፻፵፫
544 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሐ) ያለፈትን አስራ ሁለት ወራት በሚመለከተው
የመጨረሻው የሑሳብ መግለጫ መሰረት
አጠቃላይ የሀብት መጠኑ ከሃያ ሚሉዮን ብር
በታች ከሆነ ነው።
፱/ የገንዘብ ጠያቂዎች መደቦችን ከመመደብ ጋር
በተያያዘ የሚነሳ ቅሬታ የገንዘብ ጠያቂዎች
መደቦቹ አመዲደብ ለፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት
ሹም ገቢ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በአስር ቀናት
ውስጥ በተቆጣጣሪ ዲኛው ይወሰናል፤ በተቆጣጣሪ
ዲኛው የተሰጠው ውሳኔ ውሳኔው በተሰጠ በአስር
ቀናት ውስጥ ይግባኝ ላቀርብበት ይችላል።