Article text
፩/ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በሾማቸው ጉባዔ
የተጣለ ገደቦች ካለ እንደተጠበቁ ሆኖ፤ ሑሳብ
አጣሪዎች የማጣራቱን ሥራ ለማከናወን ሙለ
የሆነ ሥልጣን ይኖራቸዋል፤ በተለይም የማህበሩን
ሀብት በሙለ ለመሸጥ፣ በፍርድ ቤት ማህበሩን
ለመወከል፣ ክርክር የሚያስነሱ ጉዲዮችን በስምምነት
ወይም በግልግል ዲኝነት ለመጨረስ፣ የማህበሩን
ገንዘብ ለመሰብሰብ እና ዕዲዎችን ለመክፇል
ይችላለ።
፫፻፶፩
352 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ ሑሳብ አጣሪዎች ቀደም ሲል የነበሩ ውልችን
ለማስፇጸም ካልሆነ ወይም የሑሳብ ማጣራቱ ሥራ
ካላስገደደ በስተቀር አዱስ ሥራዎችን መጀመር
አይችለም።
፫/ ሑሳብ አጣሪዎች በሕግ፣ በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም
በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ከተሰጣቸው
ሥልጣን ውጭ በመስራታቸው በማህበሩ ወይም
በሦስተኛ ወገኖች ላይ ለሚያደርሱት ጉዲት
በአንድነትና በተናጠል ኃላፉ ይሆናለ።
፬/ ሑሳብ አጣሪዎች የማጣራቱ ሥራ ምክንያታዊ በሆነ
ጊዜ እንዱጠናቀቅ የማድረግ ኃላፉነት አለባቸው።