Article text
፪፻፶፭
256 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ ንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሥልጣን
ያለው የመንግስት አካል በአክሲዮን መዝገቡ ላይ
የተጻፈ ባለአክሲዮኖች ማህበሩን በእርግጥ
ለሚቆጣጠሩት እና ከውስጡ የገንዘብ ጥቅም
ላላቸው ሰዎች ስማቸውን ያዋሱ ስለመሆኑ በቂ
ምክንያት ያለው እንደሆነ፤ የአክሲዮኖቹ ትክክለኛ
ባለሀብቶች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ምርመራ
የሚያደርጉ ኢንስፔክተሮችን መሾም ይችላል።
፪/ ንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሥልጣን
ያለው የመንግስት አካል ቢያንስ ከማህበሩ ዋና
ገንዘብ አስር በመቶ ድርሻ ያላቸው ባለአክሲዮኖች
ጥያቄ ካቀረቡ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) መሰረት ምርመራ እንዱደረግ ማዘዝ ይችላል።