Article text
፩/ ማህበሩ የራሱ የሆኑ አክሲዮኖችን ከማህበርተኞች
መልሶ መግዛት የሚችለው፦ሀ) የባለአክሲዮኖች ጉባዔ ሲፇቅድ፤
ለ) የሚገዛበት ገንዘብ ከተጣራ ትርፍ ላይ የተነሳ
ሲሆን፤ እና
ሐ) የአክሲዮኖቹ ዋጋ ለማህበሩ በሙለ አስቀድሞ
የተከፇለ ሲሆን፤
ነው።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) መሰረት ማህበሩ
ከማህበርተኛ የገዛቸውን አክሲዮኖች ዲይሬክተሮች
ወደ ላላ ሰው ሉያስተላልፈ አይችለም፤ አክሲዮኖቹ
፩፻፸፰
179 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የሚያስገኙት ድምፅ የመስጠት መብትም ታግድ
ይቆያል።
፫/ ማህበሩ አክሲዮኖቹን የሚገዛው የባለአክሲዮኖች
አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩ ዋና ገንዘብ
እንዱቀነስ በወሰነው መሰረት ከሆነ የዚህ አንቀጽ
ንዐስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌዎች ተፇፃሚ
አይሆኑም።
፬/ ማህበሩ የራሱ የሆኑትን አክሲዮኖች ከማህበርተኞች
በመያዣነት ለመቀበል የፇለገ እንደሆነ በዚህ
አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩)
(ሀ) እና
(ሐ) ሥር
የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፇጻሚ ይሆናለ።