Article text
፩/ ማህበሩ የሁለንም ሸሪኮች ስም ወይም ቢያንስ
የሁለት ሸሪኮችን ስም የያዘ መጠሪያ ይኖረዋል፤
ከሸሪኮቹ ስም ቀጥልም “የህብረት ሽርክና ማህበር”
ተብል መጻፍ አለበት፤የማህበሩ ስም ከሸሪኮች ስም
በስተቀር ላላ ስም ሉኖርበት አይችልም።
፪/ ስሙ በማህበሩ ስም ላይ የተገለጸ ሸሪክ ከማህበሩ
የወጣ እንደሆነ የማህበሩ ስም መለወጥ አለበት።
፫/ የማህበሩ ሸሪክ ያልሆነ ሰው እያወቀ ስሙ
በማህበሩ ስም ውስጥ ሲጻፍ ያልተቃወመ
እንደሆነ እንደላልች አባላት ለማህበሩ ግዳታዎች
ኃላፉ ይሆናል።