Article text
፩/ የማህበሩን ዋና ገንዘብ ዘጠና በመቶ የሚወክለ
አክሲዮኖች በአንድ ማህበርተኛ የተያዙ እንደሆነ
አናሳ ባለአክሲዮኖች ማህበርተኛው አክሲዮኖቻቸውን
እንዱገዛቸው የመጠየቅ መብት አላቸው።
፪/ ጥያቄ አቅራቢው ባለአክሲዮን አክሲዮኖቹ
ስለሚገዙበት ሁኔታ በተለይም የአክሲዮኖቹን ዋጋ
፩፻፺፪
193 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ስለወሰነበት መንገድ መረጃ ከጥያቄው ጋር ማቅረብ
አለበት።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) መሰረት ጥያቄ
የቀረበለት ማህበርተኛ የቀረበለትን ዋጋ ያልተቀበለ
እንደሆነ ማህበሩ በተመዘገበበት ቦታ ሥልጣን
ያለው ፍርድ ቤት የአክሲዮኖቹን ዋጋ የሚወስን
ባለሞያ መሾም አለበት።
፬/ አክሲኖቹን ለመሸጥ ጥያቄ ያቀረበው ባለአክሲዮን
የአክሲዮኖቹን ዋጋ ለመወሰን የወጣውን ወጪ
መሸፇን አለበት።
፭/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፬) የተደነገገው ቢኖርም
አክሲዮን እንዱገዛ ጥያቄ የቀረበለት ማህበርተኛ
የሰጠው ዋጋ ተማኙ ባለሞያ ከወሰነው ያነሰ
እንደሆነ ወጪውን በከፉል ወይም በሙለ
እንዱሸፍን ፍርድ ቤቱ ሉያዘው ይችላል።