Article text
፩/ “ቡድን” ማለት የእናት ኩባንያ እና ተቃራኒ ድንጋጌ
እስከላለ ድረስ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር
የተመዘገቡ የሁለም ተቀጥላዎቹ ማህበራት ስብስብ
ነው።
፪/ “ተቀጥላ” ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በልላ
ኩባንያ አማካኝነት በእናት ኩባንያ ቁጥጥር ሥር
የወደቀ ኩባንያ ነው።
፫/ “እናት” ማለት በቀጥታም ሆነ በልላ ኩባንያ
አማካኝነት በተዘዋዋሪ ላላ ኩባንያን በቁጥጥር ሥር
ያደረገ ኩባንያ ነው።
፬/ ለዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) እና
(፫) ዓላማ
“ቁጥጥር” በአንቀጽ ፭፻፶፪ ሥር የተሰጠው ትርጉም
ይኖረዋል።
፬፻፩
402 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፭/ ለዚህ ርዕስ ድንጋጌዎች ዓላማ « ኩባንያ » ማለት
የአክሲዮን ማህበር፣ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል
ማህበር፤ ባለአንድ አባል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል
ማህበር እና እንደ ሁኔታው ውጭ አገር የተመዘገቡ
ከነዚህ ጋር ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸውን የንግድ
ማህበራት ያጠቃልላል።