Article text
፩/ የማህበሩን ዋና ገንዘብ ዘጠና በመቶ የሚወክለ
አክሲዮኖች በአንድ ማህበርተኛ የተያዙ እንደሆነ
ማህበርተኛው አናሳ ባለአክሲዮኖች አክሲዮኖቻቸውን
ሸጠውለት እንዱወጡ የመጠየቅ መብት አለው።
፪/ ማህበርተኛው ጥያቄውን ስለ ጠቅላላ ጉባዔ አጠራር
በተደነገገው ሥርዓት ለሚመለከታቸው ባለአክሲዮኖች
በማሳወቅ በአምስት ሳምንት ውስጥ አክሲዮኖቻቸውን
እንዱያስተላልፈለት መጠየቅ አለበት።
፫/ ማህበርተኛው አክሲዮኖቹ ስለሚገዙበት ሁኔታ
በተለይም የአክሲዮኖቹን ዋጋ ስለወሰነበት መንገድ
መረጃ ከጥያቄው ጋር ማቅረብ አለበት።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) መሰረት ጥያቄ
የቀረበለት ባለ አናሳ አክሲዮን የቀረበለትን ዋጋ
ያልተቀበለ እንደሆነ ማህበሩ በተመዘገበበት ቦታ
ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የአክሲዮኖቹን ዋጋ
የሚወስን ባለሞያ እንዱሾምለት ማመልከት ይችላል*
፭/ ባለሞያ እንዱሾም ለፍርድ ቤት ጥያቄ ያቀረበው
ባለአክሲዮን የአክሲዮን ዋጋ ለመወሰን የወጣውን ወጪ
መሸፇን አለበት።
፩፻፺፬
195 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፮/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፭) የተደነገገው ቢኖርም
አክሲዮን ለመግዛት ጥያቄ ያቀረበው ማህበርተኛ
የሰጠው ዋጋ ተማኙ ባለሞያ ከወሰነው ያነሰ እንደሆነ
ወጪውን በከፉል ወይም በሙለ ማህበርተኛው
እንዱሸፍን ፍርድ ቤቱ ሉያዝ ይችላል።
፯/ በዚህ አንቀጽ መሰረት የአናሳ ባለአክሲዮኖች መውጣት
የማህበሩን አባላት ቁጥር ከአምስት በታች ያወረደው
እንደሆነ በመብቱ የተገለገለው ባለአክሲዮን ከሶስት
ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የማህበሩን አባላት ቁጥር
መጨመር ወይም የማህበሩን ዓይነት መለወጥ አለበት።