Article text
፩/ ሽያጩ ከተፇፀመ በኋላ መቃወሚያ
የሚቀርብበት ቀን እስከሚያበቃ ፣ወይም መቃወሚያ
ቀርቦም ከሆነ የገንዘብ ጠያቂዎች መብት
በስምምነት ወይም በፍርድ ቤት እልባት
እስከሚያገኝና ለገንዘብ ጠያቂዎች እስኪከፇላቸው
ድረስ የሽያጩ ገንዘብ ለሻጭ ሳይከፇል በገዥው
እጅ ታግድ ይቆያል።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከተው
ከመፇፀሙ በፉት የተደረገ ማናቸውም ክፍያ
ወይም የመብት ማስተላለፍ ወይም ክፍያ
፹፩
82 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የመጠየቅ መብትን መተው ከሻጩ ላይ ገንዘብ
ጠያቂዎች በሆኑት ሰዎች ላይ መቃወሚያ ሉሆን
አይችልም።
፫/ በሽያጭ ውል ውስጥ ገዥው የሽያጩን ገንዘብ
በአንድ ሦስተኛ ሰው እጅ በአደራ ያስቀምጣል
ተብል ለመስማማትም ይቻላል፤ በስምምነቱ
መሰረት ገንዘቡ በአደራ ከተቀመጠ ሻጩ ለገዥው
ከሚኖርበት ተጠያቂነት ነፃ ይሆናል፤ ገዥው ይህን
በማድረግ ለሻጩ ካለበት ዕዲ ነጻ ቢሆንም ከሻጭ
ላይ ገንዘብ ጠያቂዎች ለሆኑት የሚኖርበትን
ኃላፉነት አያስቀርም።