Article text
፩/ በሥነ ሥርዓቱ ወቅት በማናቸውም ጊዜ የከሰረው
ሰው ንብረት ጠባቂ፣ ማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ፣
የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴው ወይም አንድ ዐቃቤ
ሕግ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ በልላ እንዱተካ
ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል።
፪/ ፍርድ ቤቱ በራሱ ሥልጣን የከሰረው ሰው ንብረት
ጠባቂውን በልላ ሉተካ ይችላል።
፫/ ፍርድ ቤቱ በተለይም ደግሞ የከሰረው ሰው ንብረት
ጠባቂ ከተቆጣጣሪ ዲኛው ፇቃድ ውጭ የተቀበለውን
ማንኛውንም ገንዘብ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፯፻፲ ንዐስ
አንቀጽ
(፩)
(ሰ) መሰረት በከሰረው ሰው ሀብት
ስም በተከፇተው የባንክ ሑሳብ ውስጥ ሳያስገባ
ከቀረ ወይም ከባንክ ሑሳብ ካስወጣ ፍርድ ቤቱ
በራሱ ተነሳሽነት የከሰረውን ሰው ንብረት ጠባቂ
በልላ ሉተካ ይችላል።
፭፻፹፫
584 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) የተደነገገው ቢኖርም
የገንዘብ ጠያቂዎች ኮሚቴው ወይም ከአጠቃላይ
የቅድመ ኪሣራ የገንዘብ ጥያቄዎች መጠን ውስጥ
አብዛኛው ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች የመክሰር ሥነ
ሥርዓት እንዱከፇት ያመለከተው ሰው እንዱሾም
ያቀረበውን የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ እንዱሾም
የሚደግፈ ከሆነ ፍርድ ቤቱ ማመልከቻውን ሉፇቅድ
እና ያመለከተው ሰው ያቀረበውን ሰው የከሰረው
ሰው ንብረት ጠባቂ አድርጎ ሉሾም ይችላል።