Article text
የተከራየውን ለላላ ማከራየትን ስለሚከለክለ
የውል ቃልች
፩/ በፍትሐ ብሕር ሕጉ ቁጥር ፪ሺ፱፻፶፱ የተደነገገው
ቢኖርም እንኳን ተከራዩ የንግድ መደብሩን ለገዛው
ሰው ንግደ የሚከናወንበት ቦታ የሚመለከተውን
የኪራይ ውል አያስተላልፍም ወይም የተከራይ
ተከራይ አድርጎ አያከራይም ወይም የኪራዩን ውል
ለማስተላለፍ ወይም የተከራይ ተከራይ አድርጎ
ለማከራየት የባለቤቱ ፇቃድ ያስፇልጋል የሚለ
የውል ቃልች ሁለ ዋጋ አይኖራቸውም።
፸፪
73 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ በዚህ ሕግ መፅሐፍ ሦስት ሥነ ሥርዓቶች
መሰረት ለተከራዩ ባለዕዲ የተሾሙ የመልሶ
ማደራጃ ኃላፉው ወይም ለከሰረው ሰው ንብረት
ጠባቂ የታወቁላቸውን ሥልጣን የሚነፍጉ ወይም
የሚገድቡ የውል ቃልች ዋጋ አይኖራቸውም።