Article text
፩/ ማንኛውም ክፍያ ወይም ማንኛውም ድርጊት ፇራሽ
እንዱሆን የሚሰጠው ውሳኔ ወደ ኋላ ተመልሶ
ተፇጻሚ ይሆናል።
፪/ በዓይነት ወደነበረበት መመለስ የሚቻል በማይሆንበት
ጊዜ የንብረቱ የገበያ ዋጋ ወደ ሀብቱ ይመለሳል።
፫/ ፇራሽ መሆኑ የሚመለከተው ንብረት ወይም መብት
ለሦስተኛ ወገን የተላለፇ በሚሆንበት ጊዜ ከንብረቱ
ወይም ከመብቱ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ጥሬ ገንዘብ
ፍርደ በተሰጠበት ጊዜ ባለው የገበያ ዋጋ መሰረት
ተሰልቶ ወደ ሀብቱ ይመለሳል።
፭፻፴፯
538 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ ፇራሽ መሆኑ ተጽዕኖ የሚያደርግባቸው ገንዘብ
ጠያቂዎች ፇራሽ ከመሆኑ የሚመነጩ የቅድመ
ኪሣራ የክፍያ ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላለ፤
ሆኖም በዚህ ሕግ በአንቀጽ ፮፻፷፱ መሰረት የክፍያ
ጥያቄዎቹን ማስገባት ከሚቻልበት ጊዜ ማለፍ
የለበትም።