Article text
፩/ አንድ የዲይሬክተሮች ቦርድ አባል ሥራውን
በማከናወን ላይ እያለ በሦስተኛ ወገን ስጦታም ሆነ
ላላ ዓይነት ጥቅም የተሰጠው እንደሆነ የጥቅሙ
ተጋሪ ያልሆኑ ዲይሬክተሮችን ወይም የማህበሩን
ጠቅላላ ጉባዔ ሳያስፇቅድ መቀበል አይችልም።
፪/ ስጦታውን ወይም ጥቅሙን መቀበል የጥቅም ግጭት
የሚፇጥርበት ምክንያታዊ ዕድል የላለ እንደሆነ
በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተጣለው ክልከላ
ተፇጻሚነት የለውም።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀፅ
(፩) የተጣለው ክልከላ
ከዲይሬክተርነት በተነሳ ሰው ላይም ተፇጻሚ
ይሆናል።
፪፻፳፬
225 ____________________________________________________ የንግድሕግ