Article text
፩/ ማህበሩ ስለአክሲዮን ማህበር ምስረታ የተደነገጉት
ሕጋዊ ሁኔታዎችን ሳያሟላ ተመዝግቦ መገኘቱ
ሕጋዊ ሰውነቱን እንዱያጣ አያደርገውም።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተደነገገው
ቢኖርም፤ የገንዘብ ጠያቂዎች ወይም የባለአክሲዮኖች
ጥቅም ጉዲት ላይ የሚወድቅ ከሆነ ከገንዘብ
ጠያቂዎች ወይም ከባለአክሲዮኖች አንደ
በሚያቀርበው ማመልከቻ መሰረት ፍርድ ቤት
ማህበሩ እንዱፇርስ ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ
አስፇላጊው ማስተካከያ እንዱደረግ ሉያዝ ይችላል።
ለፍርድ ቤት ማመልከቻ ማቅረብ የሚቻለው
ማህበሩ በንግድ መዝገብ ከገባበት ጊዜ አንስቶ
በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው።