Article text
፩/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው ተቀባይነት ያገኘውን
መልሶ የማደራጀት ዕቅድ የራሱን አስተያየቶች እና
ምክረ ሀሳቦች ከያዘ ሪፖርት ጋር አንድ ላይ ለፍርድ
ቤቱ ያቀርባል፤ ይህ ሪፖርት ጉዲዩ በፍርድ ቤቱ
ከመሰማቱ ቢያንስ ሦስት ቀናት አስቀድሞ ለፍርድ
ቤቱ ይቀርባል እንዱሁም የሥነ ሥርዓቱ አካል
የሆኑ ወገኖች በሙለ በቀላለ እንዱያገኙት
ይደረጋል።
፪/ ጉዲዩ በሚሰማበት ወቅት መልሶ የማደራጀት
ኃላፉው፣ ባለዕዲው እና ገንዘብ ጠያቂዎች ይሰማለ።
፫/ መልሶ የማደራጀት ዕቅደን በሚያጸድቅበት ጊዜ
ፍርድ ቤቱ የሚከተለትን ነገሮች ያረጋግጣል፡፭፻፶
551 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሀ) መልሶ የማደራጀት ዕቅደ አስፇላጊ በሆነው
አብላጫ ድምፅ መጽደቁን እና የባለዕዲውን
መክሰር የመከላከል እና የንግድ ሥራውን
አዋጭነት የማረጋገጥ ምክንያታዊ ተስፊ ያለው
መሆኑን፤
ለ) መልሶ የማደራጀት ዕቅደ “የገንዘብ ጠያቂዎች
የተሻለ ጥቅም” የሚለውን መስፇርት የሚያሟላ
መሆኑን፤
ሐ) ማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ መልሶ በማደራጀት
ዕቅደ መሰረት የሚያገኘው ጥቅም በመክሰር
ሥነ ሥርዓት ውስጥ ከሚያገኘው ያነሰ
ያለመሆኑን፤
መ) የሦስተኛ ወገኖች ጥቅሞች በተለይም ደግሞ
አዱስ የዋስትና መብቶችን ከማግኘት እና ከአዱስ
የገንዘብ አቅርቦት ማዕቀፍ አንጻር በበቂ ሁኔታ
መጠበቁን፤
ሰ) በአንቀጽ ፮፻፹፫ ንዐስ አንቀጽ
(፫) መሰረት
የተለያዩ መደቦች ተደምረው የሚገኘው ውጤት
በሚወሰድበት ጊዜ ከእነሱ በታች ደረጃ ያለው
ማንኛውም መደብ ማንኛውም ክፍያ የሚያገኝ
ወይም ማንኛውም ጥቅም የሚኖረው እንደሆነ
፭፻፶፩
552 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በመቃወም ድምጻቸውን የሰጡ የሚመለከታቸው
ገንዘብ ጠያቂዎች በተመሳሳይ ወይም በእኩል
መልኩ ሙለ ክፍያ ማግኘታቸውን፤
ረ) ተመሳሳይ ደረጃ ያላቸው የገንዘብ ጠያቂዎች
መደቦች ተመሳሳይ ወይም እኩል በሆነ መልኩ
የክፍያ ጥያቄያቸው እንደሚከፇላቸው፤
ሰ) መልሶ የማደራጀት ዕቅደን ዓላማዎች ለማሳካት
አስፇላጊ በሚሆንበት ጊዜ እና መልሶ
የማደራጀት ዕቅደ የማናቸውንም የሚመለከታቸው
ወገኖች መብቶች እና ጥቅሞች አግባብ ባልሆነ
መልኩ የማይጎዲ በሚሆንበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ
በራሱ ተነሳሽነት ከላይ
(ሰ) እና ወይም
(ረ) ውስጥ ከተመለከቱት መርሆች ውጭ የሆነ
አካሄድ ሉከተል ይችላል፤
ሸ) መልሶ በማደራጀት ዕቅደ መሰረት ማንኛውም
የሚመለከታቸው ገንዘብ ጠያቂዎች መደብ
ከሚጠይቀው ሙለ ክፍያ በላይ ሉቀበል ወይም
ይዞ ሉቆይ አይችልም።
፭፻፶፪
553 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ ዋስ የሆኑ የተፇጥሮ ሰዎች መልሶ የማደራጀት
ዕቅደን ድንጋጌዎች በማጣቀስ ጥቅማቸውን
ማስጠበቅ ይችላለ።
፭/ መልሶ የማደራጀት ዕቅደን በማረጋገጥ ወይም
ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ፍርድ በሁለም ሰው ላይ
አስገዲጅ ይሆናል፤ እንዱሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ሰፉ
ስርጭት ባለው ጋዜጣ ላይ ይታተማል።