Article text
፩/ ፍርድ ቤቱ፡ሀ) ባለዕዲው መወጣት የማይችለው የገንዘብ
ችግር ያገጠመው መሆኑ ሲረጋገጥ እና
ክፍያዎችን ያላቋረጠ ከሆነ ወይም ክፍያዎችን
ካቋረጠ አርባ አምስት ቀናት ካልሞላው
ባለዕዲው ጥያቄ በሚያቀርብበት ጊዜ፤
ለ) ባለዕዲው ክፍያዎችን ያቋረጠ ከሆነ እና
በሂደት ላይ ያለ ለጥንቃቄ ዕዲን መልሶ
የማዋቀር ሥነ ሥርዓት ከላለ፤ ማንኛውም
ገንዘብ ጠያቂ ወይም ዐቃቤ ሕግ ጥያቄ
በሚያቀርብበት ጊዜ፤
ሐ) ማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ ወይም ዐቃቤ ሕግ
የመክሰር ሥነ ሥርዓት ለመክፇት አቤቱታ
፬፻፺፬
495 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በሚያቀርቡበት ጊዜ ባለዕዲው ጥያቄ ካቀረበ
እና ክፍያ ያቋረጠበት ሁኔታ ከተፇጠረ አርባ
አምስት ቀናት እንዲልሞላው ማስረዲት
የሚችል ከሆነ፤ መልሶ የማደራጀት ሥነ
ሥርዓት ሉከፍት ይችላል።
፪/ ማንኛውም ገንዘብ ጠያቂ ወይም ዐቃቤ ሕግ
በሚያቀርበው ጥያቄ ወይም ፍርድ ቤቱ በራሱ
ሥልጣን እና ተነሳሽነት ማናቸውንም
የንብረታቸውን ክፍል በማጭበርበር ለደበቁ፣
ለማጭበርበር በማሰብ አንዲንድ ገንዘብ ጠያቂዎችን
ሳይገልጹ ለቀሩ፣ ያለምክንያት ኃላፉነታቸውን ከፍ
ላደረጉ ወይም ላልች ማናቸውንም የማጭበርበር
ተግባራት ለፇጸሙ ሐሰተኛ ባለዕዲዎች መልሶ
የማደራጀት ሥነ ሥርዓቶችን አይከፍትም።