Article text
ስለመጋበዝ
አዱስ አክሲዮኖችን ለሕዝብ ለመሸጥ የሚደረገው ጥሪ
የማህበሩ የዲይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ በፇረመበት
መግለጫ አማካኝነት ሆኖ መግለጫውም የሚከተለትን
መረጃዎች መያዝ ይኖርበታል፡፩/ የማህበሩን ስምና ዋና መሥሪያ ቤት፤
፪/ ማህበሩ በንግድ መዝገብ የተመዘገበበትን ቀን፤
፫/ የማህበሩን ዋና ገንዘብ መጠን፤ የአክሲዮኖቹን
ዓይነትና አክሲዮኖቹ ላይ የተፃፇውን ዋጋ እና
ካለም ልዩ መብት የሚያሰጡ የአክሲዮኖን
መደቦች፤
፬/ የማህበሩን ዲይሬክተሮች፣ ካለም የተቆጣጠሪ ቦርድ
አባላት፣ ሥራ አስኪያጆች እና ኦዱተሮች፤
፭ የመጨረሻውን የትርፍና ኪሣራ እንዱሁም የሀብትና
ዕዲ ሑሳብ መግለጫ እና የኦዱት ሪፖርት፤
፮/ ባለፈት የመጨረሻ አምስት ዓመታት ወይም ማህበሩ
ከአምስት ዓመታት ያነሰ ቆይታ ያለው እንደሆነ
ማህበሩ ከተመሰረተበት ቀን ጀምሮ የተከፇለትን
የትርፍ ድርሻዎች፤
፫፻፳፰
329 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፯/ ማህበሩ ያወጣቸውን የዕዲ ሰነድች፤
፰ አዱስ የወጡ አክሲዮኖችን አስመልክቶ ጉባዔው
ያስተላለፇውን ውሳኔ በተለይ አዱሶቹ አክሲዮኖች
ያላቸውን ጠቅላላ ዋጋ፣ ቁጥራቸውን፣
የተጻፇባቸውን ዋጋ፣ ዓይነታቸውንና የሚወጡበትን
ዋጋ፤
፱/ በዓይነት የተደረጉ መዋጮዎችን እና የተሰጡ ልዩ
ጥቅሞችን፤
፲/ አዱሶቹ አክሲዮኖች ትርፍ ማስከፇል የሚጀምሩበትን
ጊዜ፣ የተጣለባቸውን ገደቦች፣ እንዱሁም የተሰጡ
ልዩ መብቶችን፤
፲፩/ አክሲዮን ለመግዛት የፇረመው ሰው ግዳታ
የሚቆይበትን ጊዜ።