Article text
፩/ የውህደት ወይም የመከፇል ዕቅድ፤ የውህደት ወይም
መከፇል ሪፖርት እና ላልች አስፇላጊ የውህደት
ወይም መከፇል ሁኔታዎች በነጻ እና ገለልተኛ
ባለሞያ መገምገም አለባቸው።
፪/ በውህደቱ ወይም መከፇለ የሚሳተፈ ማህበራት
እያንዲንዲቸው የየራሳቸው ነጻ እና ገለልተኛ ገምጋሚ
ባለሙያ ይሾማለ፤ ሆኖም በውህደቱ ወይም በመከፇለ
የሚሳተፈ ማህበራት በሙለ የተስማሙ እንደሆነ
በጋራ አንድ ባለሞያ ሉሾሙ ይችላለ፤ ነጻ እና ገለልተኛ
ባለሞያው የሚሾመው በዚህ መጽሐፍ የአክሲዮን
ማህበር ኦዱተር አሿሿምን በተመለከተ በተደነገገው
ሥርዓት መሰረት ይሆናል።
፫/ በውህደቱ ወይም በመከፇለ የሚሳተፈ ማህበራት
ለግምገማው አስፇላጊ የሆኑ ሰነድችንና ላልች
አስፇላጊ መረጃዎችን ሁለ ለገምጋሚ ባለሞያዎች
ማቅረብ አለባቸው።
፬፻፳፬
425 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ ነጻ እና ገለልተኛ ገምጋሚው ለሾመው ማህበር
ባለአክሲዮኖች ወይም ሸሪኮች የሚከተለትን
በተመለከተ የራሱን አስተያየት በጽሁፍ ሪፖርት
ማቅረብ አለበት፡ሀ) በውህደቱ ወይም በመከፇለ ተካፊይ ለሆኑ
ማህበራት አባላት በለውጥ የሚሰጡትን
አክሲዮኖች ወይም ድርሻ መጠን እና ዓይነት፤
ተመኑ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ ስለመሆኑ
የራሱን አስተያየት፤
ለ) በለውጥ የሚሰጡት አክሲዮኖች ወይም ድርሻ
መጠን እና ዓይነት ተመን ለመወሰን ሥራ ላይ
የዋለው ዘዳ ወይም ቀመር ምን እንደሆነ እና
በተያዘው ጉዲይ ትክክለኛ ዘዳ ስለመሆኑ የራሱን
አስተያየት እንዱሁም በተመን አሰራሩ ሂደት
ያጋጠመ የተለየ የግምት ችግር ካለ ችግሩን
መግለጽ፤
ሐ) በውህደቱ ወይም በመከፇለ ባለመስማማታቸው
ከማህበራቱ ለሚወጡ ባለአክሲዮኖች ወይም
ሸሪኮች የሚሰጠው ክፍያ ተገቢ ስለመሆኑ፤
መ) የውህደቱ ወይም የመከፇለ ዕቅድ በጋዜጣ
ለሕዝብ ይፊ ከመደረጉ በፉት ከተሳታፉ
፬፻፳፭
426 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ማህበራት ገንዘብ የመጠየቅ መብት ያገኙ ሆኖም
የዕዲው መክፇያ ጊዜያቸው ያልደረሰ ገንዘብ
ጠያቂዎች መብት ከውህደቱ ወይም ከመከፇለ
በኋላ በቂ ጥበቃ ያለው ስለመሆኑ፤
ሰ) በውህደቱ ወይም በመከፇለ ተሳታፉ በሆኑት
ማህበራት የፊይናንስ ቁመና ምክንያት በገንዘብ
ጠያቂዎች መብት ላይ የተለየ አደጋ የተጋረጠ
እንደሆነ ይህንኑ በመግለጽ መደረግ ስላለበት
ጥበቃ።
፭/ የንግድ ማህበራት መዝጋቢው አካል የሚዋሃደትን
ማህበራት ወይም የሚከፇለውን ማህበር ዓመታዊ
የገንዘብ ዝውውር ወይም የሑሳብ ሚዛናቸውን
መነሻ በማድረግ ከተወሰነው መጠን በታች የገንዘብ
ዝውውር ወይም የሑሳብ ሚዛን ያላቸው
ማህበራትን ከውህደት ወይም ከመከፇል ግምገማ
ነጻ እንዱሆኑ መወሰን ይችላል።