Article text
፩/ የዲሬክተሮች ቦርድ አባል ለመሆን የሚችለው ቀጥል
የተመለከቱትን መስፇርቶች የሚያሟላ ሰው ነው፡ሀ) በመመስረቻ ጽሁፍ ወይም በልላ ሕግ ዝቅተኛ
ዕድሜ ተወስኖ ከሆነ የተወሰነውን ዕድሜ
የሚያሟላ፤
ለ) መልካም ሥነ-ምግባር ያለው፤
ሐ) ከዚህ በፉት በንግድ ማህበር አደራጅነት፣
ዲይሬክተርነት፣ ሥራ አስኪያጅነት፣ ተቆጣጣሪነት፣
ኦዱተርነት ወይም በላልች የአመራር ኃላፉነቶች
፩፻፺፰
199 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ላይ ተመድቦ ሲሰራ ከኃላፉነቱ ጋር በተያያዘ
ወይም በማንኛውም ላላ ሁኔታ በእምነት
ማጉደል፣ በስርቆት ወይም በውንብድና ወይም
ለቦርድ አባልነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ
ወንጀል ጥፊተኛነቱ ያልተረጋገጠ፤
መ) ላልች በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም በልላ
ሕግ የሚገለጹ መስፇርቶች ካለ እነዚህን
መስፇርቶች የሚያሟላ።
፪/ ማንኛውም ሰው አንድን ማህበር በዲይሬክተርነት
በሚመራበት ጊዜ ሥልጣኑን ከማህበሩ ጥቅም ጋር
በሚጋጭ አኳኋን በመገልገል በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ መንገድ ያልተገባ ጥቅም ማግኘቱ
የተረጋገጠ እንደሆነ ከዲይሬክተርነት መውረድ
አለበት።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩)
(ሐ) ላይ
የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ አንቀጽ ንዐስ
አንቀጽ
(፪) ላይ የተመለከተውን ጥፊት የፇጸመ ሰው
ጥፊቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ አንስቶ ለሁለት ዓመት
በማንኛውም ማህበር ዲይሬክተር መሆን አይችልም።