Article text
፩/ አንድ የንግድ ማህበር ሲፇርስና ሑሳቡ ተጣርቶ
እንዲበቃ የሑሳብ አጣሪዎች ማህበሩ ከንግድ
መዝገብ እንዱሰረዝ ለንግድ ማህበር መዝጋቢው
አካል ማመልከት አለባቸው፤ ማህበሩ ከንግድ
መዝገብ ከተሰረዘበት ዕለት በሚቀጥለው ቀን
ጀምሮ ህጋዊ ሰውነት አይኖረውም።
፪/ የንግድ ማህበሩ ከንግድ መዝገብ መሰረዝ የማህበሩ
ዋና መሥሪያ ቤት ባለበት አካባቢ ሰፉ ስርጭት
ባለው ጋዜጣ መገለፅ አለበት።