Article text
፬፻፳፯
428 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ የመዋሃድ ወይም የመከፇል ዕቅደ በጠቅላላ ጉባዔ
ከጸደቀበት ጊዜ ጀምሮ ባለት ሁለት ወራት ውስጥ
በየወሩ አንድ ጊዜ አገር ዓቀፍ ስርጭት ባለው
ጋዜጣ ለህዝብ መገለፅ አለበት፤ እንዱሁም
ማስታወቂያው በሚዋሃደት ወይም በሚከፇለው
ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት መለጠፍ አለበት።
፪/ የሚዋሃደት ማህበሮች ወይም የሚከፇለው ማህበር
ድረ-ገጽ ካለው በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) የተመለከተው ማስታወቂያ በተጨማሪ በማህበሩ
ድረ-ገጽ ላይ መውጣት ይኖርበታል።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) እና
(፪) መሰረት
ለህዝብ የሚገለጸው ማስታወቂያ የመወሃድ ወይም
የመከፇል ዕቅድ፣ የገለልተኛ ባለሞያ ሪፖርት እና
የዲይሬክተሮች ቦርድ ወይም እንደነገሩ ሁኔታ ዋና
ሥራ አስኪያጅ ያዘጋጀው ሪፖርት የሚገኙበትን
ቦታ እና አኳኋን መግለጽ አለበት፤ በተጨማሪም
ገንዘብ ጠያቂዎች ማቅረብ የሚችለትን መቃወሚያ
የሚያቀርቡበትን የጊዜ ገደብ ማመልከት አለበት።