Article text
፬፻፺፭
496 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ የሚከተለት ሰነድች ባለዕዲው መልሶ የማደራጀት
ሥነ ሥርዓት ለመክፇት ከሚያቀርበው አቤቱታ
ጋር አባሪ ሆነው መቅረብ አለባቸው፡ሀ) የንግድ ማህበሩ ሦስት የመጨረሻ የሑሳብ
ሚዛን ወረቀቶች ወይም የሑሳብ መግለጫዎች፤
ለ) የትርፍ እና ኪሣራ ሑሳብ፤
ሐ) ባለዕዲው ለመጠባበቂያ ጊዜው የሚሆን ገንዘብ
እንዲለው የሚያሳይ የገንዘብ ፍሰት መግለጫ፤
መ) የገንዘብ ጠያቂዎችን እና የባለዕዲዎችን ስም እና
አድራሻ የያዘ የሚሰበሰቡ ንግድ ነክ ገቢዎች እና
ዕዲዎች ዝርዝር።
፪/ ባለዕዲው የተሟለ ሰነድችን ለፍርድ ቤቱ ማቅረብ
የማይችልበት ሁኔታ ውስጥ ከሆነ ባለዕዲው
በአቤቱታው ውስጥ ምክንያቱን ማስረዲት አለበት።
፫/ ፍርድ ቤቱ ማናቸውንም አግባብነት ያላቸው
ተጨማሪ ሰነድች ባለዕዲው እንዱያቀርብ ሉጠይቅ
ወይም ማንኛውም ሦስተኛ ወገን በተለይም ደግሞ
፬፻፺፮
497 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ባንኮች እና የመንግስት አስተዲደር አካላት እንደዚያ
ያለ ሰነድችን እንዱያቀርቡ ሉጠይቅ ይችላል።
፬/ በገንዘብ ጠያቂዎች የሚቀርበው አቤቱታ በቃለ
መሐላ የተደገፇ ሆኖ የሚከተለትን ሰነድች ማካተት
አለበት፡ሀ) ገንዘብ ጠያቂዎቹ ጊዜው የደረሰ እና መከፇል
ያለበት ነገር ግን ያልተከፇለ የክፍያ ጥያቄ
እንዲላቸው የሚያሳይ ማስረጃ፤
ለ) ባለዕዲው ለምን ክፍያዎችን መፇጸም
እንዲልቻለ የሚያሳይ ማስረጃ፤
ሐ) ገንዘብ ጠያቂው መደበኛ የፍትሐ ብሕር
ሥርዓቶችን ተከትል በባለዕዲው ላይ ያለትን
የክፍያ ጥያቄዎች ለማስፇጸም ያልቻለባቸውን
ወይም ከዚህ በኋላ ማስፇጸም የሚችልበት
ሁኔታ ውስጥ ያልሆነባቸውን ምክንያቶች
የሚያሳይ ማስረጃ፤
መ) ባለዕዲው ክፍያ ያቋረጠበት ሁኔታ ውስጥ
መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ።