Article text
፩/ በሕግ ወይም በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ መሰረት
በጉባዔ መተላለፍ የሚችለ ውሳኔዎች በስብሰባው
ላይ ባልተገኙ፣ ድምፀ ተአቅቦ ባደረጉ፣ በሀሳብ
በተለዩ፣ ችልታ በልላቸዉ ወይም ድምፅ የመስጠት
፪፻፸፰
279 ____________________________________________________ የንግድሕግ
መብት በተከለከለ ባለአክሲዮኖች ላይ ሁለ ተፇጻሚ
ይሆናለ።
፪/ ማንኛውም በውሳኔው ጥቅሙ የተጎዲ ሰው በሕግና
በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ የተመለከቱትን
ድንጋጌዎች በመቃረን የተላለፇ ውሳኔ ውድቅ
እንዱደረግለት ውሳኔው መተላለፈን ካወቀበት ጊዜ
አንስቶ በተከታታይ ዘጠና ቀናት ውስጥ ለፍርድ
ቤት ማመልከት ይችላል፤ ሆኖም ውሳኔው በንግድ
መዝገብ የገባ ከሆነ ስለ ውሳኔው መተላለፍ
በተጨባጭ አወቀም አላወቀም ውሳኔውን
በመቃወም ለፍርድ ቤት ማመልከት የሚችለው
ውሳኔው በንግድ መዝገብ ከገባበት ቀን አንስቶ
በተከታታይ ስልሳ ቀናት ውስጥ ብቻ ነው።
፫/ ውሳኔውን ውድቅ ለማድረግ ክስ የሚቀርበው
የማህበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ቦታ
ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይሆናል።
፬/ አመልካቹ ለጊዜው ውሳኔው እንዱታገድ ጥያቄ
ለፍርድ ቤት ያቀረበ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የማህበሩን
ዋና ሥራ አስኪያጅ ወይም በክርክሩ ማህበሩን
የወከለው ላላ ሰው ሀሳብ ከሰማ በኋላ በጉዲዩ ላይ
ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ የጉባዔው ውሳኔዎች
፪፻፸፱
280 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ቢፇጸሙ በማህበሩ ወይም በክስ አቅራቢው ላይ
የማይመለስ ጉዲት ያደርሳለ ብል ሲያምን
ውሳኔዎቹ ለጊዜው እንዲይፇጸሙ ሉያግድ ይችላል።
፭/ ፍርድ ቤቱ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፬) መሰረት እግድ ቢሰጥ በማህበሩ ላይ ያልተገባ
ኪሣራ ሉያደርስ ይችላል ብል ካመነ የእግድ ጥያቄ
አቅራቢው ለኪሣራው ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና
እንዱያቀርብ ወይም ገንዘብ እንዱያስይዝ ሉያዝ
ይችላል።
፮/ የጉባዔው ውሳኔ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ከተደረገ
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሁለም የማህበሩ
ባለአክሲዮኖች ላይ ተፇጻሚ ይሆናል።
፯/ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች ሦስተኛ ወገኖች በቅን
ልቦና ያገኟቸውን መብቶች አያስቀሩም።