Article text
በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ እንዱሸጥ በፍርድ ቤት ስለ
መጽደቁ
፩/ በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያለ ድርጅት
በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ የሚሸጥ የሆነ እንደሆነ
ፍርድ ቤቱ በሚያስፇልገው አብላጫ ድምፅ በገንዘብ
ጠያቂዎች የጸደቀ መልሶ የማደራጀት ዕቅድ
ያለመኖሩን እና የአሸናፉው ተጫራች የንግድ ሥራ
ዕቅድ የንግድ ሥራውን አዋጭነት የማረጋገጥ ተስፊ
ያለው መሆኑን ያጣራል።
፪/ ፍርድ ቤቱ በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያለ
ድርጅት የንግድ ሥራውን እንዱቀጥል አስፇላጊ
የሆኑት በቀረቡት የግዢ ጥያቄዎች ውስጥ
የተዘረዘሩ ውልች እንዱተላለፈ ትዕዛዝ ይሰጣል፤
እንዱሁም በሕጉ መሰረት ስም እስከሚተላለፍ
ድረስ አሸናፉው ተጫራች ሥራ አመራሩን
እንዱረከብ ለማስቻል የንግድ ሥራው አሸናፉ
ለሆነው ተጫራች የሚተላለፍበትን ቀን ይወስናል።
፫/ ፍርድ ቤቱ አሸናፉው ተጫራች የገዛቸውን ንብረቶች
በነጻነት እንዲይተላለፈ ገደብ ሉያስቀምጥ የሚችለው
ቢበዛ ለሁለት ዓመታት ነው።
፭፻፷፩
562 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፬/ የተላለፈት ንብረቶች የሚሸጡት ከማንኛውም
ተጨባጭ፣ ቅድመ ሁኔታ ያለውም ሆነ ላላ ዓይነት
ዕዲ፣ ዕገዲ፣ ክፍያ እና ኃላፉነት እንዱሁም
በተለይም ደግሞ ከአካባቢ ክፍያዎች እና ኃላፉነቶች
ነጻ ሆነው ነው።