Article text
፩/ ማንኛውም ጉባዔ ውሳኔ ማሳለፍ የሚችለው ምልዓተ
ጉባዔው የተሟላ ሲሆንና በጉባዔው ከተገኙት
ባለአክሲዮኖች የአብላጫውን የድምፅ ድጋፍ ሲያገኝ
ነው።
፪/ ለሚተላለፈት ውሳኔዎች መሟላት ያለበት ምልዓተ
ጉባዔ የሚሰላው የማህበሩን ዋና ገንዘብ (ካፒታል)
ካቋቋሙት አክሲዮኖች አንጻር ሆኖ ለእያንዲንደ
የጉባዔ ዓይነት በዚህ ሕግ በተወሰነው መሰረት
ነው፤ በሚካሄደ ጉባዔዎች ሁለ አስፇላጊው
ምልዓተ ጉባዔ የሚታሰበው በሕግ መሰረት ድምፅ
የመስጠት መብት የላላቸው አክሲዮኖች ከተቀነሱ
በኋላ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች በማህበሩ ዋና ገንዘብ
፪፻፷፭
266 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ውስጥ ባላቸው ድርሻ ወይም መዋጮ መሰረት
ነው።
፫/ የባለአክሲዮኖች ጉባዔ ለማድረግ የሚያስፇልገውን
ምልዓተ ጉባዔና ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስፇልገውን
የድምፅ ብልጫ የሚመለከቱትን የዚህ ሕግ
ድንጋጌዎች በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ መለወጥ
አይቻልም።