Article text
፩/ በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፮ ሥር የተመለከቱት
ድንጋጌዎች ቢኖሩም የጥቅም ግጭት ያለበት ውል
የማህበሩን ሀብት አስር በመቶ ወይም ከዚያ በላይ
የሚያህል ንብረት የሚሸፍን ከሆነ ውለ እንዱደረግ
የማህበሩ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በቅድሚያ ፇቃድ
መስጠት አለበት።
፪/ ከማህበሩ ጥቅም ጋር ሉጋጭ የሚችል ጥቅም ያለው
ዲይሬክተር፣ ሥራ አስኪያጅ፣ ወይም ባለአክሲዮን
የጥቅም ግጭት መንስዔ ሉሆኑ ስለሚችለ ጉዲዮች
በተለይም የጥቅም ግጭቱ ዓይነት፣ መጠን እና
የመሳሰለትን በተመለከተ የተሟላና ትክክለኛ መረጃ
ነጻ እና ገለልተኛ ለሆነው የማህበሩ የውጭ ኦዱተር
ማቅረብ አለበት።
፪፻፹፫
284 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ የማህበሩ የውጭ ኦዱተር የጥቅም ግጭት መኖሩን
እና አለመኖሩን፣ ካለም የጥቅም ግጭቱን መንስኤ፣
ዓይነት፣ መጠን እና ከማህበሩ ጋር የጥቅም ግጭት
ያለው ዲይሬክተር፣ ባለአክሲዮን ወይም ላላ
ከማህበሩ ጋር ቅርበት ያለውን ሰው ማንነት
በመሳሰለት ጉዲዮች ላይ የተሟላ መረጃ ማጠናቀር
አለበት፤ የሰበሰበውን መረጃ እና የራሱን ምክረ ሀሳብ
ውለ ከመደረጉ በፉት ለማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ
ማቅረብ አለበት።
፬/ ከማህበሩ ጥቅም ጋር ሉጋጭ የሚችል ጥቅም
ከስምምነቱ የሚያገኝ የማህበሩ ዲይሬክተር ወይም ላላ
ሰው ባለአክሲዮን ቢሆንም ጠቅላላ ጉባዔው ስምምነቱን
በተመለከተ ሲወስን ድምፅ መስጠት የለበትም።
፭/ የማህበሩ ዲይሬክተሮች በዚህ አንቀጽ ሥር
የሚወድቅ የጥቅም ግጭት ሉፇጥር የሚችል ውል
እንዱደረግ ጠቅላላ ጉባዔው ከፇቀደበት ጊዜ አንስቶ
ዘገየ ቢባል በሰባ ሁለት ሰዓታት ውስጥ እንዱደረግ
ስለተፇቀደው ውል ዝርዝር መረጃ የያዘ ሪፖርት
ለንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ወይም አግባብነት
ላለው ላላ የመንግስት መሥሪያ ቤት ማቅረብ እና
፪፻፹፬
285 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በማህበሩ ድረ-ገጽ እንዱወጣ ማድረግ አለባቸው፤
ሪፖርቱ የሚከተለትን ማካተት አለበት፡ሀ) የሚሸጠውን ወይም የሚገዛውን ንብረት
ለይቶ ለማወቅ የሚረዲ መግለጫ፤
ለ) የሚደረገው ክፍያ ዓይነት እና መጠን፤ እና
ሐ) ከማህበሩ ጋር የጥቅም ግጭት ያለበትን
ዲይሬክተር፣ ባለአክሲዮን ወይም ላላ ከማህበሩ
ጋር ቅርበት ያለውን ሰው ስም፣ ለጥቅም
ግጭቱ መንስዔ የሚሆነው በማህበሩ እና
ከማህበሩ ጋር ውል በገባው ድርጅት ውስጥ
ያለውን ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጥቅም፤
በግልጽ ማመልከት አለበት።
፮/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) እስከ
(፭) በተመለከተው አኳኋን በባለአክሲዮኖች ጉባዔ በቅድሚያ
ተፇቅድ ሪፖርት ያልተደረግ ስምምነት አይጸናም፤
በመሆኑም በማህበሩ፣ በባለአክሲዮኖች ወይም በገንዘብ
ጠያቂዎች ጥያቄ የቀረበለት እንደሆነ ፍርድ ቤት ውለ
እንዱፇርስ ማዘዝ ይችላል፤ ፍርድ ቤቱ ውለ እንዱጸና
የሚፇቅደው ከውለ መፍረስ ይልቅ የውለ መጽናት
ለማህበሩ የበለጠ እንደሚጠቅም ግልጽ የሆነ እንደሆነ
ነው።
፪፻፹፭
286 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፯/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፮) መሰረት የቀረበው
ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ የጥቅም ግጭት ያለበት
ውል ሲፇርስ ማህበሩ በውለ ምክንያት ለደረሰበት
ጉዲት ካሣ የማግኘት መብት አለው፤ በተጨማሪም
ከማህበሩ ጋር የጥቅም ግጭት ያለበት ውል የገባው
ዲይሬክተር፣ ባለአክሲዮን ወይም በዚህ ሕግ አንቀጽ ፫፻፮ ንዐስ አንቀጽ
(፮) መሰረት ከማህበሩ ጋር
ቅርበት ያለው ላላ ሰው በውለ ምክንያት ያገኘውን
ትርፍ ከነሕጋዊ ወለደ ለማህበሩ መስጠት አለበት።