Article text
፩/ የጉባዔ ውይይት በቃለ ጉባዔ መያዝ አለበት፤ ቃለ
ጉባዔው በስብሰባው ላይ በተገኙት ዲይሬክተሮች እና
በማህበሩ ፀሐፉ ከተፇረመበት በኋላ በቃለ ጉባዔ
መዝገብ ይገለበጣል፤ ቃለ ጉባዔው ወደ መዝገብ
በትክክል ስለመገልበጡ በማህበሩ የዲይሬክተሮች
፪፻፸፭
276 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ቦርድ ሰብሳቢ ወይም በላልች ሁለት የቦርድ አባላት
መረጋገጥ አለበት።
፪/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ሥር የተመለከተው
ቢኖርም፤ ጉባዔው ሥራ ከመጀመሩ በፉት ስብሰባው
ላይ ከተገኙት ባለአክሲዮኖች መካከል በጉባዔው ላይ
የተደረገው ውይይት እና የተላላፇው ውሳኔ
በትክክል በቃለ ጉባዔ መስፇሩን አረጋግጠው
በዲይሬክተሮች ቦርድ እና በማህበሩ ፀሐፉ ምትክ
የሚፇርሙ ሦስት ባለአክሲዮኖችን መምረጥ
ይቻላል፤ እንዱህ ዓይነቱ ምርጫ በስብሰባው ጥሪ
እንደ አጀንዲ ባይያዝም ሉከናወን ይችላል።
፫/ የጉባዔው ቃለ ጉባዔዎች በተለይ ከዚህ በታች
የተመለከቱትን ጉዲዮች መያዝ አለባቸው፡ሀ) የጉባዔውን ጥሪ አደራረግ፤
ለ) የስብሰባውን ቦታና ቀን፤
ሐ) አጀንዲዎቹን፤
መ) በጉባዔው የተገኙ የቦርድ አባላትን ስም፤
ሰ) በስብሰባው ላይ የተገኙ አክሲዮኖችን ብዛትና
የምልዓተ ጉባዔውንቁጥር፤
ረ) ለጉባዔው የቀረቡትን ሰነድች፤
፪፻፸፮
277 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሰ) የውይይቱን አጭር ማጠቃለያ፤
ሸ) የተሰጡትን ድምጾች ውጤት፣ እና
ቀ) ጉባዔው ያሳለፊቸውን ውሳኔዎች፤
፬/ ምልዓተ-ጉባዔው ባለመሟላቱ ምክንያት ጉባዔው
ለመሰብሰብ ሳይችል የቀረ እንደሆነ የጉባዔው
ሰብሳቢ ይኸው በቃለ ጉባዔ እንዱያዝ ያደርጋል።