Article text
፩/ እያንዲንደ አክሲዮን ከተጣራው ዓመታዊ ትርፍ
እንዱሁም ማህበሩ ሲፇርስ ከሚቀረው የተጣራ
ንብረት ድርሻ የማግኘት መብት ይሰጣል።
፪/ በመመስረቻ ጽሁፈ ተቃራኒ ድንጋጌ ከላለ በስተቀር
የትርፍ ድርሻና ማህበሩ ሲፇርስ ከተጣራው ንብረት
የሚገኘው ድርሻ ባለአክሲዮኑ ለማህበሩ ዋና ገንዘብ
ገቢ ባደረገው ገዘብ መጠን ይታሰባል።
፫/ እያንዲንደ አክሲዮን ድምፅ የመስጠት መብት
ይሰጣል፤ ለባለአክሲዮኑ ድምፅ የሚሰጠው ክብደት
፩፻፺፩
192 ____________________________________________________ የንግድሕግ
አክሲዮኑ በማህበሩ ዋና ገንዘብ ውስጥ የሚወክለውን
መጠን መሰረት ያደረገ መሆን አለበት።
፬/ የማህበሩን ዋና ገንዘብ ለመጨመር በጥሬ ገንዘብ
ለመሸጥ የወጡ አክሲዮኖች በሚኖሩበት ጊዜ
እያንዲንደ ባለአክሲዮን በማህበሩ ውስጥ
ባለአክሲዮኑ ባለው የአክሲዮን ድርሻ መጠን
በቅድሚያ የመግዛት መብት ይኖረዋል።
፭/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፬) የተመለከተው
መብት በዚህ ሕግ አንቀጽ ፬፻፵፰ እስከ ፬፻፶፯ ሥር
ባለት ድንጋጌዎች መሰረት ተፇጻሚ ይሆናል።