Article text
፩/ የተቀጥላ ማህበር ሑሳቦች ለዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ
የሚያቀርቡት የእናት ማህበሩ ሑሳቦች
በሚያቀርቡበት ጊዜ እና ሁኔታ ይሆናል።
፪/ ለእናት ማህበሩ እና ለተቀጥላዎቹ ማህበራት አንድ
የተጠቃለለ የሀብትና ዕዲ የሑሳብ መግለጫ እና
የትርፍና ኪሣራ የሑሳብ መግለጫ መዘጋጀት
አለበት።
፫/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) የተደነገገው
ቢኖርም፤ የዲይሬክተሮች ቦርድ እንደዚህ ዓይነቱን
ሰነድ ማዘጋጀት፡፫፻፲፮
317 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ሀ) ሉሆን የማይችል ወይም እጅግ ከባድ ወይም
ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ወይም የማህበሩ
የገንዘብ ጥቅም ዝቅተኛ ከመሆኑ የተነሳ
ለባለአክሲዮኖች የማይጠቅም ከሆነ፤
ለ) እናት ማህበሩን ወይም ተቀጥላውን የሚጎዲ እና
ተቀጥላ ማህበሩ የሚያከናውነው ሥራ የተለያየ
ከመሆኑ የተነሳ እንደ አንድ ዓይነት ማህበር
የማይቆጠሩ እንደሆነና ይኸው ሀሳብ በንግድ እና
ኢንደስትሪ ሚነስቴር ወይም አግባብ ባለው
የመንግስት አካል የፀደቀ ከሆነ በዚህ አንቀጽ
ንዐስ አንቀጽ
(፪) የተደነገገው ግዳታ ተፇጻሚ
አይሆንም።