Article text
፩/ የከሰረው ሰው የዕቃ ዝርዝር መዝገብ በሚዘጋጅበት
ጊዜ ያለበትን የታክስ እና የቀረጥ ግዳታዎች
ለንብረት ጠባቂው መግለጽ አለበት።
፪/ ንብረት ጠባቂው ባለዕዲው የሰጠውን መግለጫ
ለታክስ እና ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣናት
ያስገባል።
፫/ ባለዕዲው ንብረት ጠያቂው በጠየቀው በሃያ ቀናት
ውስጥ ለመተባበር ፇቃደኛ ካልሆነ ንብረት ጠባቂው
ባለዕዲው እንቢተኛ መሆኑን ለተቆጣጣሪ ዲኛው እና
ለታክስ እና ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣናቱ
ያሳውቃል።