Article text
፩/ የማህበሩ የዲይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የጉባዔው
ሰብሳቢ ይሆናል፤ ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ
ምክትል ሰብሳቢ፣ምክትል ሰብሳቢ በማይኖርበት ጊዜ
ከዲይሬክተሮች መካከል በሹመት ቀደምትነት
ያለው፣ ቀደምትነት ያለው በማይኖርበት ጊዜ ደግሞ
ጠቅላላ ጉባዔው የሚመርጠው ሰው ሰብሳቢ
ይሆናል።
፪/ ጉባዔው የተጠራው በማህበሩ ተቆጣጣሪ ቦርድ፣
በኦዱተሮች፣ በፍርድ ቤት በተሾመ ሰው፣ በሕግ
በተፇቀደለት ላላ የመንግስት ባለሥልጣን ወይም
በመጨረሻው ሑሳብ አጣሪ የሆነ እንደሆነ የጉባዔው
ሰብሳቢ የሚሆነው ጥሪ ያደረገው አካል ነው።
፪፻፷፰
269 ____________________________________________________ የንግድሕግ