Article text
፩/ በልላ ሕግ የተለየ መጠን ካልተወሰነ በስተቀር፤
ከማህበሩ የተጣራ ትርፍ አምስት በመቶ በየዓመቱ
በሕግ ወደተወሰነው መጠባበቂያ ገንዘብ መዛወር
ይኖርበታል፤ ሆኖም ወደ መጠባበቂያው የተዛወረው
ገንዘብ መጠን የማህበሩ ዋና ገንዘብ አምስት በመቶ
ላይ ሲደርስ የማዛወሩ ተግባር አስገዲጅነት ይቀራል።
፪/ በማንኛውም ምክንያት በሕግ የተወሰነው
የመጠባበቂያ ገንዘብ በዚህ አንቀጽ በንዐስ አንቀጽ
(፩) ከተመለከተው መጠን ዝቅ ያለ እንደሆነ
፫፻፲፱
320 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ወደዚያው መጠን እንዱመለስ ገንዘብ የማዛወር
ግዳታ ተፇጻሚ ይሆናል።