Article text
፫፻፷፱
370 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፩/ በማንኛውም ምክንያት የሚደረግ የአክሲዮኖች
ዝውውር በጽሁፍ መሆን አለበት፤ ዝውውሩ
በአክሲዮኖች መዝገብ ውስጥ ካልገባ በስተቀር
በሦስተኛ ወገኖች ላይ መቃወሚያ ሉሆን
አይችልም።
፪/ በማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ተቃራኒ ድንጋጌ ከላለ
በስተቀር አክሲዮኖች በማህበሩ አባላት መካከል
ያለገደብ ሉተላለፈ ይችላለ።
፫/ አንድ ማህበርተኛ አክሲዮኑን የማህበሩ አባል ላልሆነ
ሰው ከመሸጡ በፉት ማህበርተኛ ያልሆነው ሰው
ያቀረበለትን ዋጋ በመግለጽ አክሲዮኖቹን በዚያው
ዋጋ እና ሁኔታ እንዱገዙት ለማህበሩ አባላት ዕድል
መስጠት አለበት።
፬/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፫) ሥር የተመለከተው
ማስታወቂያ ለማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ በደረሰ
በአስራ አምስት ቀናት ባለአክሲዮን በሆነ ሰው
የውል ሀሳቡ ተቀባይነት ካላገኘ ባለአክሲዮኑ
ማህበርተኛ ያልሆነው ሰው ያቀረበለትን የውል
ሀሳብ መቀበል ይችላል።