Article text
፩/ የንግድ ማህበራት የሚፇርሱበትን ሁኔታ
የሚመለከቱት ጠቅላላ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ሆኖ ማህበሩ የሚፇርሰው በሚከተለት
ምክንያቶች ነው፡ሀ) ሸሪኮች ማህበሩ እንዱፇርስ በሙለ ድምፅ
ሲስማሙ፤
ለ) ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ሲሆን
ከሸሪኮች አንደ እንዱፇርስ ለማህበሩ ጥያቄ
ያቀረበ እንደ ሆነ፤
ሐ) ሁለም የማህበሩ ድርሻዎች በአንድ አባል የተያዙ
እንደሆነ፤
መ) ማህበሩ አንዱቀጥል የሚያደርግ ተቃራኒ
ስምምነት ከላለ በስተቀር ከማህበሩ ሸሪኮች
፩፻፵፰
149 ____________________________________________________ የንግድሕግ
አንደ የሞተ ወይም የከሰረ ወይም ችልታ ያጣ
እንደሆነ፤
ሰ) በማህበርተኞች መካከል በሚደረግ ውል ለሥራ
አስኪያጁ ማህበሩን ለማፍረስ ሥልጣን ተስጥቶት
ከሆነ ሥራ አስኪያጁ ማህበሩ እንዱፇርስ
ሲወስን።
፪/ ማንኛውም ተቃራኒ ስምምነት የዚህ አንቀጽ ንዐስ
አንቀጽ
(፩) ድንጋጌን ተፇጻሚነት የሚያስቀር
አይሆንም።