Article text
፩/ የንግድ ማህበር ማለት ሰዎች መዋጮ አዋጥተው
በህብረት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በመሰማራት
ከሚገኘው ትርፍ ተካፊይ ለመሆን በመመስረቻ
ጽሁፍ አማካኝነት የሚያቋቋሙት ማህበር ነው።
፪/ የዚህ አንቀፅ ንዐስ አንቀፅ
(፩) ድንጋጌ ቢኖርም
የእሽሙር ማህበር የሚቋቋመው ማህበርተኞች
በመካከላቸው በሚያደርጉት በሦስተኛ ወገኖች
በማይታወቅ ውል አማካኝነት ነው።
፫/ የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) ድንጋጌ ቢኖርም
ባለአንድ አባል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
የንግድ ማህበር ነው።