Article text
፩/ የዚህ ሕግ አንቀጽ ፮፻፸ በመክሰር ሥነ ሥርዓት
ላይ በተመሳሳይ ተፇጻሚ ይሆናል።
፪/ የመጨረሻ ክፍያው በሚሰላበት ጊዜ ዋስትና ሰጪው
ለገንዘብ ጠያቂው የፇጸመው ማንኛውም ክፍያ
ከግምት ውስጥ ይገባል።
፫/ የመክሰር ሥነ ሥርዓቱ በሚመለከታቸው በርካታ
ዋስትና ሰጪዎች በአንድነት እና በነጠላ የተሰጠ
ዋስትና ያለው የክፍያ ጥያቄ የያዘ ገንዘብ ጠያቂ
በቅድመ ኪሣራ የክፍያ ጥያቄው ዋጋ ልክ የቅድመ
ኪሣራ የክፍያ ጥያቄዎቹን በሁለም ሥነ ሥርዓቶች
ውስጥ ማቅረብና በእያንዲንደ ሥነ ሥርዓት ውስጥ
በሚደረጉትም ክፍያዎች ሁለ ገንዘቡን በሙለ
እስኪያገኝ ድረስ ተካፊይ ለመሆን ይችላል።
፬/ አንድ ዋስትና ሰጪ ለገንዘብ ጠያቂው የከፇለ እና
በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) መሰረት የቅድመ
ኪሣራ የክፍያ ጥያቄውን ያላቀረበ እንደሆነ ገንዘብ
ጠያቂው መብቱ በታወቀለት ገንዘብ መጠን ልክ
፮፻፳፱
630 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ካልሆነ በስተቀር በሚደረጉ ክፍያዎች መብቱ
አይታወቅለትም።