Article text
፩/ ከማህበሩ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ቢያንስ አስር በመቶ
ድርሻ ባላቸው ባለአክስሲዮኖች ጥያቄ የቀረበለት
እንደሆነ የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ወይም
አግባብ ያለው ላላ የመንግስት መሥሪያ ቤት
የማህበሩ ሥራ አመራር አነስተኛ የአክሲዮን ድርሻ
ያላቸውን ማህበርተኞች ወይም ማህበሩን በሚጎዲ
አኳኋን መከናወኑን እና አለመከናወኑን መርምረው
ሪፖርት የሚያቀርቡ አንድ ወይም ከአንድ በላይ
የሆኑ ኢንስፔክተሮች መሾም አለበት።
፪፻፶፩
252 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ አመልካቹም ማመልከቻ ለቀረበለት አካል አስፇላጊ
ናቸው የሚላቸውን ሰነድች እና ላላ ማስረጃ
መጠቆም አለበት።
፫/ የምርመራውን ወጪ የሚሸፍኑት ጥያቄ አቅራቢዎቹ
ናቸው፤ ሆኖም የምርመራው ውጤት የደረሰውን
ጥቆማ ትክክለኛነት የሚያስረዲ ሆኖ ከተገኘ ማህበሩ
ለጥያቄ አቅራቢዎቹ ለምርመራው ያወጡትን ገንዘብ
መመለስ ይኖርበታል።