Article text
ኃላፊነቶች
መልሶ በማደራጀት ሥነ ሥርዓቱ ወቅት መልሶ
የማደራጀት ኃላፉው የሚከተለው ሥልጣን እና
ኃላፉነቶች አለት፡፩/ መደበኛ የሥራ ሂደቱን ማከናወንን በተመለከተ
ባለዕዲውን መቆጣጠር፤
፪/ የባለዕዲው ንብረት የሚገኝበትን ትክክለኛ ቦታ
ለማወቅ የሚያስችለውን መረጃ ከመንግስት
ባለሥልጣን አካላት፣ ከማህበራዊ ዋስትና ተቋማት፣
ከብድር ተቋማት እና ከላልች ተቋማት መቀበል፤
፭፻፩
502 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ የንብረቶቹን ዝርዝር በማዘጋጀት ረገድ ባለዕዲውን
መቆጣጠር፤
፬/ መልሶ የማደራጀት ዕቅደን በማዘጋጀት ረገድ
ባለዕዲውን ማገዝ፤
፭/ አግባብ በሚሆንበት ጊዜ የገንዘብ ጠያቂዎች
መደቦችን ማዋቀር፤
፮/ የንግድ ሥራ እንቅስቃሴው በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ
የንግድ ሥራ እንዱሸጥ ማዘጋጀት፤
፯/ ከባለዕዲው መደበኛ የሥራ ሂደት ውጭ
የሚቀበለውን ማናቸውንም ገንዘብ በንብረቱ ስም
የሚከፇት የባንክ ሑሳብ ውስጥ ገቢ ማድረግ፤
፰/ የቅድመ ኪሣራ ጥያቄዎችን እንዱቀበል ወይም
ውድቅ እንዱያደርግ ለተቆጣጣሪ ዲኛው ሀሳብ
ማቅረብ፤
፱/ የገንዘብ ጠያቂዎች መደብ ስብሰባ ወይም የገንዘብ
ጠያቂዎች ጠቅላላ ጉባዔ ከመደረጉ ቢያንስ አምስት
ቀናት አስቀድሞ ለፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት ሹም
ገቢ የሚደረግ የባለዕዲውን ጉዲዮች እና ተግባራት
የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
፲/ የገንዘብ ጠያቂዎች መደቦች ስብሰባ ወይም የገንዘብ
ጠያቂዎች ጠቅላላ ጉባዔ ከመደረጉ ቢያንስ አምስት
ቀናት አስቀድሞ ለፍርድ ቤቱ መዝገብ ቤት ሹም
፭፻፪
503 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ገቢ የሚደረግ ለባለዕዲዎች የቀረቡ ዋስትናዎችን
ጨምሮ የተዘጋጁትን የተለያዩ መልሶ የማደራጀት
ዕቅድች የተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት አዘጋጅቶ
ማቅረብ፤
፲፩/ የገንዘብ ጠያቂዎች መደብ ስብሰባዎችን ወይም
የገንዘብ ጠያቂዎች ጠቅላላ ጉባዔዎችን
በሉቀመንበርነት መምራት፤
፲፪/ በተለይም የባለዕዲውን የፊይናንስ ሁኔታ እና የንግድ
ሥራ ዕቅድ ኦዱት እንዱያደርጉ እና የባለዕዲውን
የንብረት ዝርዝር እና የዋጋ ግምት እንዱያዘጋጁ
ራሳቸውን የቻለ ባለሞያዎችን እንዱሾም
ለተቆጣጣሪ ዲኛው ጥያቄ ማቅረብ፤
፲፫/ የሚሰጠው አገልግልት በተቋረጠ በሰላሳ ቀናት
ውስጥ ወይም በጣም ቢዘገይ ሥነ ሥርዓቱ
በተቋረጠ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ለፍርድ ቤቱ
ሪፖርት ማቅረብ።