Article text
፩/ አዱሶቹን አክሲዮኖች መግዛት የሚጀመርበት ቀን
ቢያንስ ግዥ ከሚጀመርበት ከአስር ቀናት አስቀድሞ
አገር ዓቀፍ ስርጭት ባለው ጋዜጣ እና አመቺ በሆነ
የኤላክትሮኒክስ ዘዳ አማካኝነት ባለአክሲዮኖች
እንዱያውቁት መደረግ አለበት፤ ማስታወቂያው
የባለአክሲዮኖቹን የቀደምነት መብት፣ አዱስ
አክሲዮኖችን መግዛት የሚጀመርበትንና
የሚያልቅበትን ቀን፣ አክሲዮኖች የሚወጡበትን ዋጋ
እና ወዱያውኑ ተከፊይ መሆን የሚገባውን
የአክሲዮን ዋጋ መጠን መግለጽ ይኖርበታል።
፫፻፴፬
335 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ አክሲዮኖቹ በስም የተመዘገቡ ከሆነ ማህበሩ
የአክሲዮን ሽያጭ ከመጀመሩ አስር ቀናት በፉት
ማስታወቂያውን በተመዘገበ ደብዲቤ ለባለአክሲዮኖቹ
መላክ ይችላል።