Article text
፩/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ አክሲዮኖች እንዱከፇለ
ጥሪ የማድረግ እና ቃል የተገቡት ገንዘቦች የመክሰር
ፍርደ በተሰጠበት ቀን የመክፇያ ጊዜያቸው ያልደረሰ
ቢሆንም ባለአክሲዮኖች እና ማህበርተኞች ቃል
የገቡትን ገንዘብ እንዱከፍለ የማዘዝ ሥልጣን አለው።
፪/ ባለአክሲዮኖች እና ማህበርተኞች በከሰረው ሰው
ንብረት ጠባቂ ማሳወቂያ በተሰጣቸው በአስር ቀናት
ውስጥ ቃል የገቡትን ገንዘብ ያልከፇለ እንደሆነ
የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ የከሰረውን ሰው
ንብረት በመወከል ቃል የተገቡትን ገንዘቦች
ለማስከፇል ሕጋዊ እርምጃ ይወስዲል።