Article text
፩/ እያንዲንደ ገንዘብ ጠያቂ መልሶ የማደራጀት ሥነ
ሥርዓት እንዱከፇት ፍርድ በተሰጠ በአራት ወራት
ውስጥ ራሱ ወይም በወኪለ አማካኝነት በአደራ
፭፻፳፩
522 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ደብዲቤ ወይም ተቀባዩ ለመቀበለ ማረጋገጫ
ሉሰጥበት በሚችል ላላ ማንኛውም ኤላክትሮኒክ
መንገድ መልሶ ለማደራጀት ኃላፉው በመላክ የቅድመ
ኪሣራ የክፍያ ጥያቄዎቹን ያቀርባል፤ ይህ የጊዜ
ገደብ ልዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ በተቆጣጣሪ ዲኛው
ሉራዘም ይችላል።
፪/ ገንዘብ ጠያቂዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ ውስጥ
የሚከተለትን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡ሀ) ዋና ክፍያውን እና አግባብ ከሆነ ወለደን
እንዱሁም የመክፇያ ጊዜው የደረሰበትን ወይም
የሚደርስበትን ቀን በመግለጽ የቅድመ ኪሣራ
የክፍያ ጥያቄውን መጠን፤
ለ) የመጠባበቂያ የክፍያ ጥያቄዎችን በተመለከተ
የክፍያ ጥያቄውን መጠን ግምት፤
ሐ) የቅድመ ኪሣራ ክፍያው የቀረበበትን የሕግ
አግባብ፤
መ) የገንዘብ ጠያቂውን ስም፣ አድራሻ እና የባንክ
ዝርዝር መረጃ፤
ሰ) አለኝ የሚለትን ማንኛውንም ቅድሚያ
የማግኘት መብት እና ቅድሚያ የማግኘት
መብቱን የሕግ አግባብነት፤
፭፻፳፪
523 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ረ) ከቅድመ ኪሣራ የክፍያ ጥያቄው ጋር በተያያዘ
አለኝ የሚለትን ማንኛውንም የንብረት ዋስትና
ወይም ባለሀብትነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ
የሚደረጉ የሽያጭ ውልች እና አለኝ የሚለት
የንብረት ዋስትና የሚሸፍናቸውን ንብረቶች፣
ዋስትናው የተሰጠበትን ቀን እና ዋስትናው
የተመዘገበ ከሆነ የምዝገባ ቦታውን እና
የምዝገባ ቁጥሩን፤
ሰ) የቅድመ ኪሣራ የክፍያ ጥያቄን የሚመለከት
ማንኛውንም የግል ዋስትና፣ የዋስትና
ሰጪዎቹን ስም እና አድራሻ፣ የዋስትናውን
መጠን፣ የተሰጠበትን ቀን እና ዋስትናው
በተናጠል፣ በአንድነት ወይም በአንድነትና
በተናጠል መሆኑን፤
ሸ) ማንኛውም ሉጠየቅ የሚችል ማቻቻል፤
የሚጠየቅ ከሆነ መልሶ የማደራጀት ሥነ
ሥርዓት የተከፇተበት ቀን ላይ በሁለቱም
ወገኖች በኩል ያለትን የክፍያ ጥያቄዎች
መጠን፣ ክፍያዎቹ የመክፇያ ጊዜያቸው
የደረሰበትን ቀን እና ከማቻቻል በኋላ
የሚቀረውን የገንዘብ መጠን።
፭፻፳፫
524 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፫/ ገንዘብ ጠያቂዎች የክፍያ ጥያቄያቸውን የሚደግፈ
ሰነድችን ማቅረብ አለባቸው፤ ለሚያቀርቧቸው
ማስረጃዎችም ደረሰኝ ይሰጣቸዋል።
፬/ መልሶ የማደራጀት ኃላፉው መልሶ የማደራጀት ሥነ
ሥርዓቱ ከተዘጋ በኋላ ማስረጃዎቹን ይመልሳል
እንዱሁም ከአንድ ዓመት በኋላ ማስረጃዎቹን
ለመመለስ ኃላፉ አይሆንም።
፭/ በዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) በተቀመጠው የጊዜ
ገደብ ውስጥ የቅድመ ኪሣራ የክፍያ ጥያቄያቸውን
እና የዋስትና መብታቸውን ያላቀረቡ ገንዘብ
ጠያቂዎች በክፍፍለ ውስጥ መሳተፍ አይችለም፤
እንዱሁም በንግድ ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ያለ ድርጅት
በመንቀሳቀስ ላይ እንዲለ የተሸጠ እንደሆነ የክፍያ
ጥያቄያቸው ለባለሀብቱ ላቀርብ አይችልም።