Article text
ለጥንቃቄ ዕዲን መልሶ በማዋቀር ሥነ ሥርዓቱ ወቅት
መደበኛ የሥራ ሂደቱ በባለዕዲው ይዞታ ውስጥ ይሆናል
እንዱሁም ባለዕዲው በመደበኛ የሥራ ሂደት ውስጥ
የሚወድቁ ማናቸውንም ውሳኔዎች የማስተላለፍ ሥልጣን
አለው፤ ሆኖም አብዛኛውን ንብረት እንደመሸጥ እና
የዋስትና መብት እንደመፍጠር ያለ ከመደበኛ የሥራ ሂደት
ውጭ የሆኑ ማናቸውም ውሳኔዎች ዕዲን መልሶ በማዋቀር
ዘርፍ ባለሞያው አስቀድመው መጽደቅ አለባቸው።