Article text
፩/ የአክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖችን መዝገብ
በዋናው መሥሪያ ቤት መያዝ አለበት፤ መዝገቡ
፩፻፸፮
177 ____________________________________________________ የንግድሕግ
በወረቀት ወይም ለረጅም ዘመን በሚቆይ
የኤላክትሮኒክ ዘዳ መያዝ ይችላል።
፪/ መዝገቡ የባለአክሲዮኖችን ስም፣ አድራሻ፣ዜግነት፣
የአክሲዮኖችን ብዛትና መለያ ቁጥር፣ የተከፇለውን
ገንዘብ መጠንና ባለአክሲዮኖቹ የተመዘገቡበትን ቀን
መያዝ አለበት።
፫/ ባለአክሲዮኖችና የሚያገባቸው የመንግስት መሥሪያ
ቤቶች መዝገቡን በነፃ መመልከት ይችላለ፤
ባለአክሲዮን ያልሆነ ላላ ሰው መዝገቡን ማየት
የሚችለው ለዚህ ተብል ማህበሩ የወሰነውን
የአገልግልት ክፍያ ሲፇጽም ነው።
፬/ ማንኛውም ሰው የተወሰነውን የአገልግልት ክፍያ
ሲፇጽም የመዝገቡን ግልባጭ ወይም በአጭር
የተውጣጣ ጽሁፍ እንዱሰጠው ማህበሩን መጠየቅ
ይችላል፤ ማህበሩ ጥያቄው በቀረበ በአስራ አምስት
ቀናት ውስጥ ግልባጩን ወይም በአጭር
የተውጣጣውን ጽሁፍ ለጠያቂው መሰጠት
አለበት።
፭/ ጥቅም ካለው ማንኛውም ሰው ወይም
ከባለአክሲዮን ጥያቄ ሲቀርብለት አግባብ ያለው
፩፻፸፯
178 ____________________________________________________ የንግድሕግ
የመንግስት አካል በመዝገቡ አጻጻፍ ላይ የተፇጠረ
ስህተት እንዱታረም ማድረግ ይችላል።
፮/ የአክሲዮን መዝገቡ ዝርዝር በትክክል ባለመጻፈ
ምክንያት ለሚደርስ ማንኛውም ጉዲት
የዲይሬክተሮች ቦርድ አባላት በአንድነትና በተናጠል
ኃላፉዎች ይሆናለ።