Article text
፩/ የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፪) እስከ
(፮) ያለት
ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ሕግ ከአንቀጽ ፮፻፶፬ እስከ አንቀጽ ፮፻፶፯ ያለት ድንጋጌዎች
በኪሣራ ሥነ ሥርዓት ላይ ተፇጻሚነት
ይኖራቸዋል።
፮፻፲፰
619 ____________________________________________________ የንግድሕግ
፪/ የተፇጥሮ ሰዎችን ጨምሮ ዋስትና ሰጪዎች
በመክሰር ሥነ ሥርዓት ውስጥ በተናጠል ክፍያ
ለማስፇጸም የሚደረጉ ክርክሮች እንዱቋረጡ
መጠየቅ አይችለም።
፫/ ንብረቱ ለዕዲ መያዣ በአንድ ገንዘብ ጠያቂ ይዞታ
ውስጥ የሚገኝ ካልሆነ በስተቀር የከሰረው ሰው
ንብረት ጠባቂ ለዕዲ ማስያዣነት የዋለ ንብረቶችን
ጨምሮ ማናቸውንም ንብረቶች ለመሸጥ ሥልጣን
አለው።
፬/ ለዕዲ ማስያዣነት የዋለ ንብረት በይዞታው ውስጥ
የሚገኘው ገንዘብ ጠያቂ የንብረት የዋስትና መብቱን
ተጠቅሞ ንብረቱን ሉሸጥ ወይም በራሱ ሥልጣን
የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ ንብረቱን እንዱሸጠው
ሉፇቅድ ይችላል ፤ለዕዲ ማያዣ የዋለው ንብረት
ከክፍያ ጥያቄው በላይ በሆነ ዋጋ ዋስትና ባለው
ገንዘብ ጠያቂ የተሸጠ እንደሆነ እላፉው በከሰረው
ሰው ንብረት ጠባቂ ይሰበሰባል፤ የተሸጠበት ዋጋ
ከክፍያ ጥያቄው በታች ከሆነ ገንዘብ ጠያቂው
፮፻፲፱
620 ____________________________________________________ የንግድሕግ
ለተቀረው ገንዘብ ዋስትና እንደላለው ገንዘብ ጠያቂ
የክፍያ ጥያቄውን ሉያቀርብ ይችላል።
፭/ የከሰረው ሰው ንብረት ጠባቂ የመክሰር ሥነ
ሥርዓት እንዱከፇት ፍርድ በተሰጠ በስድስት ወራት
ውስጥ ለዕዲ ማስያዣነት የዋለ ንብረቶችን ለመሸጥ
እርምጃዎችን ሳይወስድ የቀረ እንደሆነ ባለሀብትነቱ
እንደ ተጠበቀ ሆኖ የተፇጸመ የሽያጭ ውል ያላቸው
ገንዘብ ጠያቂዎችን ጨምሮ በግልጽ በተቀመጡ
የከሰረው ሰው ንብረቶች ዋስትና ያላቸው ማናቸውም
ገንዘብ ጠያቂዎች የንብረት የዋስትና መብታቸውን
ተግባራዊ ሉያደርጉ ይችላለ።
፮/ የዚህ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ
(፩) እንደተጠበቀ ሆኖ
በዚህ ሕግ አንቀጽ ፯፻፶፩ እና አንቀጽ ፯፻፶፪
መሰረት ከከሰረው ሰው ንብረት ውስጥ ዕቃዎችን
የማስመለስ መብት ያላቸው ገንዘብ ጠያቂዎች
ሉያስመልሱ ይችላለ።